ምሳሌ 3:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእኔ ትምህርት ረጅም ዕድሜን ከብዙ ተድላና ደስታ ጋር ይሰጥሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀኖችን ይጨምሩልሃል፤ ዓመቶችንም ያረዝሙልሃል፤ ሕይወት፣ ሀብትንና ሰላምን ያበዙልሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ብዙ ቀኖች፥ የሕይወት ዓመታትና ሰላምም ይጨምሩልሃልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብዙ ዘመናትንና ረጅም ዕድሜን ሰላምንም ይጨምሩልሃልና። |
ይህን ብታደርግ እግዚአብሔር አምላክህ ለቀድሞ አባቶችህ ሊሰጣቸው በመሐላ ቃል በገባላቸው ምድር የአንተና የልጆችህ ዘመን ከምድር በላይ እንዳለው ሰማይ ይረዝማል።
በሰውነት ማጠንከሪያ ትምህርት ራስን ማለማመድ ጥቅሙ ጥቂት ነው፤ እግዚአብሔርን ማምለክ ማለማመድ ግን ለአሁንና ለሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው ለሁሉ ነገር ይጠቅማል።