ዘኍል 8:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካነጻሓቸውና ከቀደስካቸውም በኋላ ሌዋውያን በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ለማገልገል ብቃት ይኖራቸዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ሌዋውያኑን ካነጻሓቸውና እንደሚወዘወዝ መሥዋዕት አድርገህ ካቀረብሃቸው በኋላ አገልግሎታቸውን ለመፈጸም ወደ መገናኛው ድንኳን ይመጣሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ካነጻሓቸውና ለመወዝወዝም ቁርባን ካቀረብካቸው በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ለመፈጸም ይገባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የምስክሩን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፤ ስጦታም አድርገህ በፊቴ ታቀርባቸዋለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም በኋላ ሌዋውያን የመገናኛውን ድንኳን አገልግሎት ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ፤ ታነጻቸውማለህ፥ ስጦታም አድርገህ ታቀርባቸዋለህ። |
“እነሆ ሌዋውያን የእኔ አገልጋዮች ናቸው፤ የግብጻውያንን በኲር ሁሉ በገደልኩ ጊዜ ከያንዳንዱ እስራኤላዊ የሚወለደውን በኲርና ከእንስሶቹም በኲር የሆነውን ሁሉ ለእኔ የተለየ እንዲሆን አድርጌ ነበር፤ አሁን ግን በኲር ሆነው የሚወለዱትን ወንዶች ልጆች የራሴ በማድረግ ፈንታ ሌዋውያንን መርጬአለሁ፤ እነርሱ የእኔ አገልጋዮች ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”