ዘኍል 31:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምስቱንም የምድያም ነገሥታት ኤዊን፥ ሬቄምን፥ ጹርን፥ ሑርንና ሬባዕን ገደሉ፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም ገደሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተገደሉትም መካከል ዐምስቱ የምድያም ነገሥታት ኤዊ፣ ሮቆም፣ ሱር፣ ሑርና ሪባ ይገኙባቸዋል፤ የቢዖርን ልጅ በለዓምንም በሰይፍ ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድያምንም ነገሥታት በዚያው ጦርነት በአንድነት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሮባቅ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በዚያው ጦርነት በሰይፍ ገደሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከተገደሉትም ጋር የምድያምን ነገሥታት ገደሉአቸው፤ አምስቱም የምድያም ነገሥታት ኤዊ፥ ሮቆም፥ ሱር፥ ሑር፥ ሪባ ነበሩ፤ የቢዖርንም ልጅ በለዓምን ደግሞ በሰይፍ ገደሉት። |
ሞአባውያን ለምድያማውያን ሽማግሌዎች “ይህ የምታዩት የሕዝብ ብዛት በሬ በመስክ የሚገኘውን ሣር ሁሉ ጠራርጎ እንደሚበላ በዙሪያችን ያለውን ነገር ሁሉ ጠራርጎ የሚያጠፋ ነው” አሉአቸው። ስለዚህ በዚያን ጊዜ የሞአብ ንጉሥ የነበረው የጺጶር ልጅ ባላቅ፥
በዓማው ምድር በኤፍራጥስ ወንዝ አጠገብ በፐቶር ከተማ ይኖር ወደነበረው ወደ ቢዖር ልጅ ወደ በለዓም ይጠሩት ዘንድ መልእክተኞች እንዲህ ብሎ ላከበት፤ “ከግብጽ የወጣ አንድ ሕዝብ ምድሪቱን ሁሉ ሸፍኖአታል፤ እነርሱም በአቅራቢያችን ሰፍረዋል፤
እንደ ትቢያ ብዛት ያላቸውን የያዕቆብ ዘሮች ማን ሊቈጥር ይችላል ወይስ እንደ አዋራ ብናኝ ብዛት ያለውን የእስራኤልን ሩብ ብዛት ማን ሊገምት ይችላል? የጻድቃንን ሞት እንድሞት አድርገኝ መጨረሻዬንም እንደ እነርሱ አድርገው።”
በመጨረሻም በለዓም ባላቅን “እነሆ፥ እኔ ወደ ራሴ ሕዝብ ተመልሼ መሄዴ ነው፤ ነገር ግን ከመሄዴ በፊት የእስራኤል ሕዝብ ወደ ፊት በሕዝብህ ላይ የሚያደርጉትን በመግለጥ ላስጠነቅቅህ እወዳለሁ” ካለው በኋላ፥
ይህንንም የምታደርጉት እናንተን በፔዖር በማታለል ግፍ ስለ ሠሩባችሁና በፔዖር በወረደው መቅሠፍት ምክንያት በተገደለችው በአለቃቸው ልጅ በኮዝቢ አማካይነት በፈጸሙት ሽንገላ ነው።”
በፔዖር ሳለን የበለዓምን ምክር ተቀብለው ሕዝቡ በእግዚአብሔር ላይ ያላቸውን እምነት እንዲተዉ ያደረጉ ሴቶች መሆናቸውን ዘነጋችሁን? በእግዚአብሔር ሕዝብ ላይ የአባር ቸነፈር መቅሠፍት ያመጣም ያ ስሕተት ነበር።
እነርሱ የቀናውን መንገድ ትተው ጠፍተዋል፤ ክፉ በመሥራት የሚገኘውን ገንዘብ የወደደውን የቢዖርን ልጅ የበለዓምን መንገድ ተከትለው ተሳስተዋል።
ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከእርሱም ጋር በፊቱ ብዙ ተአምራት ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ፤ እርሱ የአውሬው ምልክት የነበረባቸውንና ለአውሬውም ምስል ይሰግዱ የነበሩትን ተአምራት እያደረገ ያስታቸው ነበር፤ እነዚህ ሁለቱ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ከነሕይወታቸው ተጣሉ።
ነገር ግን የምነቅፍብህ አንዳንድ ነገሮች አሉኝ፤ ይኸውም የበለዓምን ትምህርት የያዙ አንዳንድ ሰዎች በመካከላችሁ አሉ፤ ይህ በለዓም የእስራኤል ሕዝብ ለጣዖት የተሠዋውን ምግብ በመብላትና ዝሙት በማድረግ እንዲሰናከሉ ባላቅን የመከረ ነው።