ሉቃስ 20:39 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሕግ መምህራንም አንዳንዶቹ “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርክ!” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንዳንድ ጸሐፍትም፣ “መምህር ሆይ፤ መልካም ተናገርህ” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው “መምህር ሆይ! መልካም ተናገርህ፤” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከጻፎችም ወገን የሆኑ ሰዎች፥ “መምህር ሆይ፥ መልካም ብለሃል” ብለው መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከጻፎችም አንዳንዶቹ መልሰው፦ መምህር ሆይ፥ መልካም ተናገርህ አሉት። |
በዚህ ጊዜ ታላቅ ሁካታ ሆነ፤ ከፈሪሳውያን ወገን የሆኑ አንዳንድ የሕግ መምህራንም ተነሡና “እኛ በዚህ ሰው ላይ ምንም ክፉ ነገር አላገኘንበትም፤ መንፈስ ወይም መልአክ ተናግሮት ይሆናል፤ እኛ ምን እናውቃለን?” በማለት ተከራከሩ።