ኢዩኤል 3:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ በፍርድ ሸለቆ ፍርድ የሚሰጥበት ቀን ደርሶአል፤ ስለዚህ ቊጥሩ እጅግ የበዛ ሕዝብ በዚያ ተሰብስቦአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ ሕዝብ፣ በጣም ብዙ ሕዝብ፣ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ ተሰብስቧል፤ ፍርድ በሚሰጥበት ሸለቆ፣ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቧልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቧልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና ውካታዎች በፍርድ ሸለቆ ተሰሙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእግዚአብሔር ቀን በፍርድ ሸለቆ ቀርቦአልና የብዙ ብዙ ሕዝብ ውካታ በፍርድ ሸለቆ አለ። |
በተራሮች ላይ የሚሰማውን ጩኸት አድምጡ፤ ይህም ጩኸት በአንድነት የተሰበሰቡ የብዙ ሕዝብ መንግሥታት ሁካታ ነው፤ የሠራዊት አምላክ ሠራዊቱን ለጦርነት እያዘጋጀ ነው፤
እግዚአብሔር እንደ ነጐድጓድ ያለ ድምፁን በሠራዊቱ ላይ ያሰማል፤ ሠራዊቱ ምንኛ ብዙ ነው! ትእዛዙን የሚቀበሉ ከቊጥር በላይ ናቸው፤ በእርግጥም የእግዚአብሔር ቀን ታላቅ ነው፤ በጣም አስፈሪ ስለ ሆነ በዚያ ቀን ማን ችሎ ይቆማል?
አሕዛብን ሁሉ ሰብስቤ፥ ወደ ኢዮሣፍጥ ሸለቆ አወርዳቸዋለሁ፤ የእኔ የሆኑትን ሕዝቤን እስራኤልን በሕዝቦች መካከል ስለ በታተኑና ምድሪቱን ስለ ተካፈሉ በኢዮሣፍጥ ሸለቆ ወደ ፍርድ አቀርባቸዋለሁ።
ታላቁ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ አመጣጡም እየፈጠነ ነው፤ ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ቀን የሚሰማው ድምፅ አስከፊ ነው፤ ተዋጊው በከፍተኛ ድምፅ ይጮኻል።