የጥበብን መንገድ ባለመሻት፥ ጥሩውን ለማወቅ ካለመቻላቸው በላይ የስሕተታቸውን መታሰቢያ ጥለው አልፈዋል፤ በዚህም ገበናቸውን ሁሉም ያየዋል።
እነዚህ ጥበብን የተላለፉ ናቸውና ደግ ነገርን ባለማወቅ የደረሰባቸውን መዓት በማወቅ እንደ እነዚያ የጠፉ ብቻ አይደለም። ነገር ግን የበደሉትን በደል መሰወር እንዳልተቻላቸው መጠን ለስንፍናቸው መታሰቢያን በዚህ ዓለም ተዉ።