ትእዛዛትን ከሚፈጽመው ጻድቅ ሰው፥ ነፍሱ ነፍስህን ከምትመስለው ሰው፥ ብትበድል እንኳ ከሚያዝንልህ ሰው ዘንድ አትራቅ።
ሃይማኖት እንዳለው ከምታውቀው፥ እግዚአብሔርንም ከሚፈራ፥ ልቡናውም እንደ ልብህ ከሆነ ጻድቅ ሰው ጋር ምክርህን ተናገር፤ ብታዝንም ከአንተ ጋር ያዝናል።