ሕጉን የሚፈጽም ብዙ መባ እንዳቀረበ ይቆጠርለታል። ትእዛዛቱን የሚያከብር የኀብረት መሥዋዕቶችን ያቀርባል።
አለቃም አድርገው ቢሾሙህ ራስህን አታኵራ፤ ከእነርሱ እንደ አንዱ ሁን፤ ኀዘናቸውንም እዘን፤ ተቀምጠህም ፍረድላቸው።