ቅርንጫፉ በበዛ ዛፍ ላይ እንደሚበቅል ቅጠል፥ አንዳንዶቹ ይወድቃሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ ያድጋሉ፤ የሥጋና የደም ትውልዶች እንደዚሁ ናቸው፤ አንዱ ሲሞት ሌላው ይወለዳል።
ቅጠሉ ጭፍቅ ያለ የእንጨት ቅጠል የመጀመሪያው ቅጠል እንዲረግፍ የኋላውም እንዲለመልም፤ ደማዊና ሥጋዊ ፍጥረት ሁሉ እንዲሁ ነው፤ ይህ ይወለዳል ያም ይሞታል።