አራሾች በጀርባዬ ላይ አረሱ፥ ትልማቸውን አስረዘሙ።
ዐራሾች ጀርባዬን ዐረሱት፤ ትልማቸውንም አስረዘሙት።”
ጀርባዬን በጅራፍ ተልትለው፥ የታረሰ ማሳ አስመስለውታል።
አቤቱ፥ ኀጢአትንስ ብትጠባበቅ፥ አቤቱ፥ ማን ይቆማል?
ጐሽ እንዲተልምልህ ልታጠምደው ትችላለህን? ወይስ ከአንተ በኋላ በእርሻ ላይ ይጐለጉላልን?
በምድር ላይ እንደ ተሰነጠቀ እንደ መሬት ጓል፥ እንዲሁ አጥንቶቻችን በሲኦል ተበተኑ።
ጀርባዬን ለገራፊዎች፥ ጉንጬንም ለጠጉር ነጪዎች ሰጠሁ፤ ፊቴንም ከውርደትና ከትፋት አልመለስሁም።
ነፍስሽንም፦ “በአንቺ ላይ እንድንረማመድ ዝቅ በዪ” በሚሉአት በአስጨናቂዎችሽ እጅ አኖረዋለሁ፤ ጀርባሽንም ለሚሻገሩት እንደ መሬትና እንደ መንገድ አደረግሽላቸው።