ምሳሌ 17:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በድሀ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ይሰድባል፥ በጥፋትም ደስ የሚለው ሳይቀጣ አይቀርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤ በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በድኾች ብታፌዝ የፈጠራቸውን እግዚአብሔርን እንደ ሰደብክ ይቈጠራል፤ በሌላው ሰው ላይ በሚደርሰው መከራ ብትደሰት አንተም ትቀጣለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በድሃ የሚያላግጥ ፈጣሪውን ያነሣሣዋል፥ በሚጠፋም ላይ ደስ የሚለው ከፍርድ አይነጻም፥ የሚራራ ግን ምሕረትን ያገኛል። |
ለአሞንም ልጆች እንዲህ በላቸው፦ የጌታ እግዚአብሔርን ቃል ስሙ፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ መቅደሴ በረከሰ ጊዜ፥ የእስራኤልም ምድር ባድማ በሆነች ጊዜ፥ የይሁዳም ቤት ተማርከው በተወሰዱ ጊዜ እሰይ ብለሻልና፤