ዘኍል 34:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፋፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚያከፋፍሏችሁ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ናቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ ምድሪቱን በሕዝቡ መካከል ያከፋፍሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድሪቱን ርስት አድርገው የሚከፍሉላችሁ ሰዎች ስማቸው ይህ ነው፤ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ። |
የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያከፋፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ።