እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
ማቴዎስ 25:36 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ታምሜ ጠይቃችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታርዤ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ አስታምማችሁኛል፤ ታስሬ ጠይቃችሁኛል።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታርዤ ነበር፥ አልብሳችሁኛል፤ ታምሜ ነበር፥ ጠይቃችሁኛል፤ ታስሬ ነበር መጥታችሁ ጐብኝታችሁኛል።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፤ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታምሜ ጠይቃችሁኛልና፥ ታስሬ ወደ እኔ መጥታችኋልና። |
እንጀራህንስ ለተራበ እንድትቈርስ፥ ስደተኞቹን ድሆች ወደ ቤትህ እንድታስገባ፥ የተራቈተውን ብታይ እንድታለብሰው፥ ከሥጋ ዘመድህ እንዳትሸሽግ አይደለምን?
የደከሙትን አላበረታችሁም፥ የታመመውን አላከማችሁትም፥ የተሰበረውን አልጠገናችሁትም፥ የባዘነውን አልመለሳችሁትም፥ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቆና ገዛችኋቸው።
እንዲሁ እየደከማችሁ ድውዮችን ልትረዱና እርሱ ራሱ ‘ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ብፁዕ ነው፤’ እንዳለ የጌታን የኢየሱስን ቃል ልታስቡ ይገባችሁ ዘንድ በሁሉ አሳየኋችሁ።”
በሰማይ የበለጠና ፍጻሜ የሌለው ሀብት እንዳላችሁ በማወቃችሁ፥ የንብረታችሁን መነጠቅ በደስታ ተቀበላችሁ፤ በእስራት ላይ የነበሩትን የስቃያቸው ተካፋይ ሆናችሁ።
በእግዚአብሔር አብ ፊት ንጹሕና ያልረከሰ አምልኮ፥ “አባትና እናት የሞቱባቸውን ልጆች፥ እንዲሁም ባሎቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች በችግራቸው መርዳት፥ ራስንም ከዓለም ርኲሰት መጠበቅ ነው።”