ማርቆስ 5:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ እንደገና በጀልባ ወደ ማዶ በተሻገረ ጊዜ፥ ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰባሰበ፤ በባሕሩም አጠገብ እንዳለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ እንደ ገና በጀልባ ወደ ማዶ በተሻገረ ጊዜ፣ ብዙ ሕዝብ በዙሪያው ተሰባሰበ፤ በባሕሩ ዳርቻም እንዳለ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ በጀልባ ወደ ባሕሩ ማዶ እንደገና በተመለሰ ጊዜ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ በዚያ ጊዜ እርሱ በባሕሩ አጠገብ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ በባሕርም አጠገብ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፥ በባሕርም አጠገብ ነበረ። |
እንደገናም በባሕር ዳርቻ ያስተምር ጀመረ። እጅግ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ ስለ ተሰበሰቡ እርሱ በባሕሩ ላይ በነበረች ጀልባ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም ሁሉ በባሕሩ ዳርቻ ነበሩ።