ማርቆስ 2:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጾሙ አይችሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም፣ እንዲህ አላቸው፤ “ሙሽራው ከእነርሱ ጋራ እያለ ዕድምተኞቹ ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋራ እያለ ሊጾሙ አይችሉም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር እያለ ሚዜዎች መጾም ይገባቸዋልን? አይደለም! ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ መጾም አይገባቸውም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጾሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጾሙ አይችሉም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም አላቸው፦ ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሚዜዎች ሊጦሙ ይችላሉን? ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ ሊጦሙ አይችሉም። |
ኢየሱስም እንዲህ አላቸው “ሙሽራው ከእነርሱ ጋር ሳለ እድምተኞች ሊያዝኑ ይችላሉን? ነገር ግን ሙሽራው ከእነርሱ የሚወሰድበት ጊዜ ይመጣል፤ በዚያን ጊዜ ይጾማሉ።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር። መጥተውም “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጾሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ስለ ምንድነው?” አሉት።