ሉቃስ 9:57 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም በመንገድ ሲሄዱ ሳሉ አንድ ሰው ኢየሱስን፦ “አንተ ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ፤” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመንገድ ሲሄዱም አንድ ሰው ቀርቦ፣ “ወደምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ጒዞ ቀጥለው በመንገድ ላይ ሳሉ አንድ ሰው ኢየሱስን “እኔ ወደምትሄድበት ሁሉ ልከተልህ እፈልጋለሁ፤” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ በመንገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፥ “መምህር፥ ወደምትሄድበት ልከተልህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም በመንገድ ሲሄዱ አንድ ሰው፦ ጌታ ሆይ፥ ወደ ምትሄድበት ሁሉ እከተልሃለሁ አለው። |