ሉቃስ 2:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በጌታ ሕግ እንደተባለው፦ “ሁለት ዋኖሶችን ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶችን” መሥዋዕት ለማቅረብ ወደ ኢየሩሳሌም መጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደግሞም በጌታ ሕግ፣ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች እንደ ተባለ፣” መሥዋዕት ለማቅረብ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በጌታ ሕግ “ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች ለመሥዋዕት ማቅረብ ይገባል” የሚል ትእዛዝ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔርም ሕግ እንደ ታዘዘ ሁለት ዋኖስ ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ስለ እርሱ መሥዋዕት አድርገው ያቀርቡለት ዘንድ። |
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገር፦ ሴት ፀንሳ ወንድ ልጅም ብትወልድ፥ ሰባት ቀን ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ እንደ ወር አበባዋም ጊዜያት ትረክሳለች።
“እርሱም ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባይኖረው፥ ስለ ሠራው ኃጢአት እንደ ቁርባኑ አድርጎ የኢፍ መስፈሪያ አሥረኛ ክፍል መልካም ዱቄት ለኃጢአት መሥዋዕት ያመጣል፤ የኃጢአት መሥዋዕት ነውና ዘይት አያፈስበትም፥ ዕጣንም አይጨምርበትም።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ቸር ስጦታ ታውቃላችሁ፤ ሀብታም ሲሆን፥ እናንተ በእርሱ ድህነት ባለ ጠጎች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ድሀ ሆነ።