ያለፈውን፥ የአሁኑንና የወደፊቱን አንተ ሠርተሀል፤ አሁን ያለውንና በኋላ የሚመጣውን አንተ ቀርጸሃል፤ አንተ ያሰብከው ሆኗል።
ከዚህ አስቀድሞና ከዚያም በኋላ የሆነውን አንተ አድርገሃልና የዛሬውንና የሚመጣውንም ታውቀዋለህ፤ አንተም በምታውቀው ሆነ።