መጽሐፈ ዮዲት 7:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤሳው ልጆችና የአሞን ልጆች ወጥተው በዶታይም ትይዩ ባለው ተራራማ አገር ሰፈሩ፤ ከእነሱም አንዳንዶቹን በሞኹር ወንዝ አጠገብ በኩሲ አቅራቢያ ወዳለው ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ አቅጣጫ ወደ ኤግሬቤ ላኩ፤ የቀሩት የአሦር ወታደሮች ሜዳ ላይ ሰፈሩ፥ ምድርን በሙሉ ሸፈኗት፤ ድንኳኖቻቸውና ጓዛቸው እጅግ ሰፊ ቦታ ያዘ፥ እጅግም ብዙ ሆኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤሳውና የአሞን ልጆችም ወጥተው በዶታይም አንጻር ባሉ ተራሮች ሰፈሩ፤ ከእነርሱም በምኩር ወንዝ ባለ በኩሲ አጠገብ ባለ በኤቄሬቢን አንጻር ወደ ደቡብና ወደ ምሥራቅ ሰዎችን ላኩ። የቀሩት የአሦር ሠራዊቶች ግን በምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ሀገሩንም ሁሉ አለበሱት፤ ከዚህም በኋላ ጓዛቸውን ከእነርሱ የሚበዛ የሌለ ሠራዊታቸውንና ብዙ ገንዘባቸውን አጓዙ። |