መጽሐፈ ዮዲት 1:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአምባው የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ፥ በኤፈራጥስ፥ በጤግራን፥ በሄዳስጴን ያሉ ሁሉ፥ በኤለሜዖን ንጉሥ በአርዮክ ግዛት ያሉ ሁሉ ከናቡከደነፆር ጋር ወገኑ፥ ብዙ ሕዝቦችም የካሉድን ልጆች ለመውጋት ተሰበሰቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምባ የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ወጥተው ተቀበሉት፤ በኤፍራጥስና በጤግሮስ፥ በሒደስጶንም፥ በኤሊሜዎን ንጉሥ በአርዮክ ግዛት አውራጃ ያሉ ሁሉ የካሉድን ልጆች ይዋጓቸው ዘንድ እጅግ ብዙ የሆኑ አሕዛብም ተሰበሰቡ። |