መጽሐፈ ዮዲት 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ናቡከደነዖር በምድሪቱ ሁሉ ላይ እጅግ ተቆጣ፥ የኪልቅያን፥ የደማስቆን፥ የሶርያን አገሮች እንደሚበቀል፥ በሞዓብን ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ የአሞንን ልጆች፥ ይሁዳን በሙሉ፥ እስከ ሁለት ባሕሮች ጠረፍ ድረስ በግብጽ የሚኖሩትንም ሁሉ በሰይፍ እንደሚገድል በዙፋኑና በመንግሥቱ ማለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ናቡከደነፆርም በዚያች ምድር ላይ ፈጽሞ ተቈጣ፤ የቂልቅያንና የደማስቂኒስን፥ የሶርያንም አውራጃ ሁሉ ይበቀልና በሞዓብ ምድር የሚኖሩትን ሁሉ፥ የአሞንንም ልጆች ይሁዳንም ሁሉ በግብፅ የሚኖሩትንም ከሁለቱ ባሕሮች ድረስ ተበቅሎ በሰይፍ ያጠፋቸው ዘንድ በዙፋኑና በመንግሥቱ ማለ። |