መሳፍንት 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስቲ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ታዲያ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ ይዘው እዚያው መሻገርያው ላይ ይገድሉታል፤ በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺህ ኤፍሬማውያን ተገደሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እስኪ “ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ ቃሉን በትክክል ማለት ሳይችል ቀርቶ “ሲቦሊት” ካለ፣ ይዘው እዚያው እመልካው ላይ ይገድሉታል። በዚያ ጊዜም አርባ ሁለት ሺሕ ኤፍሬማውያን ተገደሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እስቲ ሺቦሌት” በል ይሉታል፤ እርሱ ግን “ሺ” የሚለውን ፊደል አስተካክሎ መናገር ስለማይችል “ሲቦሌት” ይላል፤ ከዚህ በኋላ እርሱን ይዘው የዮርዳኖስ መሸጋገሪያ ከሆኑት ስፍራዎች በአንዱ ይገድሉታል፤ ያንጊዜም በዚሁ ዐይነት አርባ ሁለት ሺህ የኤፍሬም ሰዎች ተገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም፥ “አሁን ሺቦሌት በሉ” አሉአቸው፤ እነርሱም አጥርተው መናገር አልቻሉምና፥ “ሲቦሌት” አሉ፤ ይዘውም በዮርዳኖስ መሸጋገርያ አረዱአቸው፤ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ፦ አሁን ሺቦሌት በል አሉት፥ እርሱም አጥርቶ መናገር አልቻለምና፦ ሲቦሌት አለ፥ ይዘውም በዮርዳኖስ መሻገርያ አረዱት፥ በዚያም ጊዜ ከኤፍሬም አርባ ሁለት ሺህ ሰዎች ወደቁ። |
በዚያ ቀን ከኤፍራጥስ ወንዝ አንሥቶ እስከ ግብጽ ደረቅ ወንዝ ጌታ እህሉን ይወቃል፥ እናንተም የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ አንድ በአንድ ትሰበሰባላችሁ።
እርሱ ግን ሐሳባቸውን አውቆ እንዲህ አላቸው “እርስ በርስዋ የምትከፋፈል መንግሥት ሁላ ትጠፋለች፤ እርስ በርስዋ የምትከፋፈል ከተማ ወይም ቤት ሁላ አትቆምም።
እርሱ ግን አሁንም ካደ። ከጥቂት ጊዜ በኋላ፥ በዚያ የቆሙት ሰዎች ጴጥሮስን፥ “የገሊላ ሰው እንደ መሆንህ መጠን፥ በእርግጥ አንተ ከእነርሱ አንዱ ነህ” አሉት።
ገለዓዳውያን ወደ ኤፍሬም የሚያሻግሩትን የዮርዳኖስን መሻገሪያዎች ያዙ፤ ታድያ አምልጦ የሚሸሽ አንድ ኤፍሬማዊ ለመሻገር በሚጠይቃቸው ጊዜ፥ የገለዓድ ሰዎች “አንተ ኤፍሬማዊ ነህ?” ብለው ይጠይቁታል፤ ያም ሰው፥ “አይደለሁም” ብሎ ከመለሰላቸው፥