ኢያሱ 14:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያከፋፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ካህኑ አልዓዛር፣ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል የየነገዱ ጐሣ አባቶች የደለደሉላቸው፣ እስራኤላውያንም በከነዓን ምድር የወረሱት ርስት ይህ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌ ልጅ ኢያሱና የእስራኤል ነገድ የቤተሰብ አለቆች በከነዓን ምድር ለእስራኤላውያን አከፋፍለዋቸው የተቀበሉት ርስት ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያወረሱአቸው ርስት ይህ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የእስራኤልም ልጆች በከነዓን ምድር የወረሱት፥ ካህኑ አልዓዛርና የነዌ ልጅ ኢያሱ የእስራኤልም ልጆች ነገድ የአባቶቻቸው አለቆች ያካፈሉአቸው ርስት ይህ ነው፥ |
ርስት አድርጋችሁ ምድሪቱን በዕጣ በምታካፍሉበት ጊዜ ከምድሪቱ የተቀደሰውን ክፍል መባ አድርጋችሁ ወደ ጌታ ታቀርባላችሁ። ርዝመቱ ሀያ አምስት ሺህ ክንድ ወርዱም ሀያ ሺህ ክንድ ይሆናል፤ በዳርቻው ዙሪያ ሁሉ የተቀደሰ ይሆናል።
ይሁን እንጂ ዮርዳኖስን ስትሻገሩና ጌታ አምላካችሁ ርስት አድርጎ በሚሰጣችሁ ምድር ስትቀመጡ፥ ያለ ሥጋት እንድትኖሩ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ ሁሉ ያሳርፋችኋል።
በተራራማውም አገር የሚኖሩትን ሁሉ ከሊባኖስ ጀምሮ እስከ ማሴሮን ድረስ ሲዶናውያን ሁሉ፥ እኔ ራሴ እነዚህን ከእስራኤል ልጆች ፊት አባርራቸዋለሁ፤ እንዳዘዝሁህም ምድራቸውን ለእስራኤል ብቻ ርስት አድርገህ አካፍላቸው።
ካህኑ አልዓዛር፥ የነዌም ልጅ ኢያሱ፥ የእስራኤልም ልጆች ነገዶች የአባቶች አለቆች በጌታ ፊት በሴሎ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ አጠገብ በዕጣ ያከፋፈሉት ርስት ይህ ነው። ምድሪቱንም አከፋፍለው ጨረሱ።