እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”
ኢዮብ 39:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጉልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ በእርሱ ትታመናለህን? አድካሚ ሥራህን ለእርሱ ትተዋለህን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጕልበቱ ብርቱ ስለ ሆነ ትተማመንበታለህ? ከባዱን ሥራህንስ ለርሱ ትተዋለህ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ ብርቱ ጥንካሬው በእርሱ ትተማመናለህን? ከባድ ሥራህንስ ለእሱ ትተውለታለህን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጕልበቱስ ብርቱ ስለሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጕልበቱስ ብርቱ ስለ ሆነ ትታመነዋለህን? ተግባርህንስ ለእርሱ ትተዋለህን? |
እግዚአብሔርም አለ፦ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፥ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።”
እግዚአብሔርም ባረካቸው፥ እንዲህም አላቸው፦ ብዙ፥ ተባዙ፥ ምድርንም ሙሉአት፥ ግዙአትም፥ የባሕርን ዓሦችና የሰማይን ወፎች በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ግዙአቸው።
እንስሶች፥ ወፎች፥ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና ዓሣዎች ሁሉ እናንተን በመፍራትና በመደንገጥ ይኑሩ፤ ሁሉም በሥልጣናችሁ ሥር ይሁኑ።
ነገር ግን፦ “በፈረስ ላይ ተቀምጠን እንሸሻለን እንጂ እንዲህ አይሆንም” አላችሁ፥ ስለዚህም ትሸሻላችሁ፤ ደግሞም፦ “በፈጣን ፈረስ ላይ እንቀመጣለን” አላችሁ፥ ስለዚህም የሚያሳድዷችሁ ፈጣኖች ይሆናሉ።
በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።