ኢዮብ 23:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በታላቅ ኃይሉ ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? ይልቁንም! ማዳመጥ ይበቃው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታላቅ ኀይሉ ከእኔ ጋራ ይሟገት ይሆን? አይደለም፤ ይልቁን ያደምጠኛል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ታዲያ፥ እግዚአብሔር በታላቅ ኀይሉ ይፋረደኝ ይሆን? አይደለም፤ ነገር ግን ነገሬን ያዳምጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኀይሉ ብዛት ቢመጣብኝም እንኳ በቍጣው አያስፈራራኝም ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በኃይሉ ብዛት ከእኔ ጋር ይምዋገት ነበርን? እንኳን! ያደምጠኝ ነበር። |