ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱ ትወጣለች፥ እርሱስ ወዴት አለ?
ሰው ግን ይሞታል፤ ክንዱንም ይንተራሳል፤ ነፍሱም ትወጣለች፤ ከእንግዲህስ የት ይገኛል?
ሰው ግን ሞቶ እንዳልነበረ ይሆናል፤ ከሞተ በኋላስ የት ይገኛል?
ሰው ግን ከሞተ ፈጽሞ ይተላል፤ ሟች ሰው ከሞተ በኋላ እንግዲህ አይኖርም።
ሰው ግን ይሞትና ይጋደማል፥ ሰውም ነፍሱን ይሰጣል፥ እርሱስ ወዴት አለ?
ያዕቆብም ትእዛዙን ለልጆቹ ተናግሮ በፈጸመ ጊዜ እግሮቹን በአልጋ ላይ ሰብስቦ ሞተ፥ ወደ ወገኖቹም ተሰበሰበ።
አባቶቻችንም ሁሉ እንደ ነበሩ እኛ በፊትህ እንግዶችና መጻተኞች ነን፤ ዘመናችንም በምድር ላይ እንደ ጥላ ነው፥ አይጸናም።
“ስለምን ከማኅፀን አወጣኸኝ? ዐይን ሳያየኝ ምነው በሞትሁ።
የክፉዎች ዐይን ግን ትጨልማለች፥ የሚሸሹበትንም ያጣሉ፥ ተስፋቸውም ነፍስን አሳልፎ መስጠት ነው።”
ቢመረምራችሁስ መልካም ይሆንልችኋልን? ወይስ በሰውን እንደምታታልሉ ልታታልሉት ትፈልጋላችሁን?
ሰውም እንዲሁ ተኝቶ አይነሣም፥ ሰማይ እስኪያልፍ ድረስ አይነቃም፥ ከእንቅልፉም አይነሣም።
በውኃ ሽታ ያቈጠቁጣል፥ እንደ አትክልት ቅርንጫፍ ያወጣል።
ይህ ቁርበቴም ከጠፋ በኋላ፥ በዚያን ጊዜ ከሥጋዬ ተለይቼ እግዚአብሔርን እንደማይ አውቃለሁ።
እንደ ፋንድያ ለዘለዓለም ይጠፋል፥ ያዩትም፦ ወዴት ነው ያለው? ይላሉ።
በማኅፀን ሳለሁ ስለምን አልሞትሁም? ከሆድስ በወጣሁ ጊዜ ስለምን ፈጥኜ አልጠፋሁም?
አሁን ተኝቼ ዝም ባልሁ ነበር፥ አንቀላፍቼ ባረፍሁ ነበር፤
ስለምን መተላለፌን ይቅር አትልም? ኃጢአቴንስ ስለምን አታስወግድልኝም? አሁን በምድር ውስጥ እተኛለሁ፥ ትፈልገኛለህ፥ እኔ ግን የለሁም።”
ኀጥእ በክፋቱ ይደፋል፥ ጻድቅ ግን በእውነቱ ይታመናል።
ሁሉ ወደ አንድ ቦታ ይሄዳል፥ ሁሉም ከአፈር ነው ሁሉም ወደ አፈር ይመለሳል።
የሰው ልጆች መንፈስ ወደ ላይ እንደሚወጣ የእንስሳም ነፍስ ወደ ታች ወደ ምድር እንደምትወርድ የሚያውቅ ማን ነው?
ኢየሱስ እንደገና በታላቅ ድምፅ ጮኾ መንፈሱን ሰጠ።
ያን ጊዜም በእግሩ አጠገብ ወደቀች፤ ሞተችም፤ ጐበዞችም ሲገቡ ሞታ አገኙአት፤ አውጥተውም በባሏ አጠገብ ቀበሩአት።