ኤርምያስ 11:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ስምሽን፦ “በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ” ብሎ ጠራው፤ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር፣ የተዋበ ፍሬ ያላት፣ የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎሽ ነበር፤ አሁን ግን በታላቅ ዐውሎ ነፋስ ድምፅ፣ እሳት ያነድድባታል፤ ቅርንጫፎቿ ይሰባበራሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ጊዜ እናንተ በፍሬ እንደ ተመላ የወይራ ዛፍ ነበራችሁ፤ ነገር ግን በቅርብ ጊዜ እንደ ነጐድጓድ የሚያስተጋባ ድምፅ በማሰማት ቅጠሉን በእሳት አቃጥላለሁ ቅርንጫፎችንም እሰባብራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበችና የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፤ ከመቈረጥዋም ድምፅ የተነሣ በላይዋ እሳት ነደደባት፤ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር ስምሽን፦ በመልካም ፍሬ የተዋበች የለመለመች የወይራ ዛፍ ብሎ ጠራው፥ በጽኑ ዐውሎ ነፋስ ጩኸት እሳትን አነደደባት፥ ቅርንጫፎችዋም ተሰብረዋል። |
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ቁጣዬና መዓቴ በዚህ ስፍራ ላይ፥ በሰውና በእንስሳ ላይ፥ በዱር ዛፎችና በምድር ፍሬ ላይ ይወርዳል፤ ይነድዳል፥ አይጠፋምም።”