ዘፀአት 39:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀሚሱ መካከል አንገትጌ ነበረ፤ እንዳይቀደድም አንገትጌው ዙሪያውን ተጠልፎ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም እንደ ክሳዱ ቅድ ከቀሚሱ መካከል ላይ ዐንገትጌ ነበረው፤ እንዳይተረተርም በዐንገትጌው ዙሪያ ላይ ቅምቅማት ነበረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቀሚሱም ማጥለቂያ አንገትጌ እንዳይተረተር ታጥፎ ዙሪያውን የተዘመዘመ ነበር፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀሚሱም መካከል አንገትጌ ነበረ፤ እንዳይቀደድም በአንገትጌው ዙሪያ በአንድነት የተያያዘ ጥልፍ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀሚሱም መካከል አንገትጌ ነበረ፤ እንዳይቀደድም እንደ ጥሩር የተሠራ ጥልፍ በአንገትጌው ዙሪያ ነበረ። |