ዘፀአት 29:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀደሰው ሥጋ ወይም ቂጣ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ስለሆነ አይበላም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከክህነቱ የአውራ በግ ሥጋ ወይም ከቂጣው እስከ ንጋት ድረስ ቢተርፍ አቃጥለው፤ የተቀደሰ ስለ ሆነ መበላት የለበትም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሥጋውም ሆነ ከኅብስቱ ሳይበላ ተርፎ ያደረ ቢኖር በእሳት ይቃጠል፤ የተቀደሰ ስለ ሆነም መበላት የለበትም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቅድስናው መሥዋዕት ሥጋ ወይም እንጀራ እስከ ነገ ቢተርፍ፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ነውና አይበላም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የተካኑበትም ሥጋ ወይም እንጀራ ተርፎ ቢያድር፥ የቀረውን በእሳት ታቃጥለዋለህ፤ የተቀደሰ ነውና አይበላም። |
ለክህነት ሥርዓት የቀረበ አውራ በግ ነውና የበጉን ስብ፥ ላቱን፥ ሆድ ዕቃውን የሚሸፍነውን ስብ፥ በጉበቱ ላይ ያለውን መረብ፥ ሁለቱን ኩላሊቶቹ፥ በላያቸውም ያለውን ስብና የቀኙን ወርች ትወስዳለህ።
የማንሣት ቁርባን ነውና ከእስራኤል ልጆች ዘንድ የአሮንና የልጆቹ ድርሻ ይሁን፤ የእስራኤል ልጆች የሚያቀርቡት የሰላም መሥዋዕታቸው የማንሣት ቁርባን ይሆናል፤ ለጌታ የማንሣት ቁርባን ይሆናል።
ሙሴም የኃጢአት መሥዋዕት ስለ ሆነው ፍየል አጥብቆ ጠየቀ፥ እነሆም ተቃጥሎ ነበር፤ ሙሴም የተረፉትን የአሮንን ልጆች አልዓዛርንና ኢታምርን እንዲህ ብሎ ተቆጣ፦