ዘፀአት 25:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታቦቱን በእነርሱ ለመሸከም በታቦቱ ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አስገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መሎጊያዎችንም መሸከሚያ እንዲሆኑ በታቦቱ ማእዘኖች ላይ ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህንም መሎጊያዎች በታቦቱ አራት ማእዘን ባሉት ቀለበቶች ውስጥ አስገባ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለታቦቱ መሸከሚያ በታቦቱ ጎን ባሉት አራት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አግባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለታቦቱ መሸከሚያ በታቦቱ ጎን ባሉት ቀለበቶች መሎጊያዎቹን አግባ። |
በዚያን ጊዜም ዳዊት እንዲህ አለ፦ “የእግዚአብሔርን ታቦት እንዲሸከሙ፥ ለዘለዓለሙም እንዲያገለግሉት ጌታ ከመረጣቸው ከሌዋውያን በቀር ማንም የጌታን ታቦት ሊሸከም አይገባውም።”
ከአክሊሉ በታች ሁለት የወርቅ ቀለበቶችን አድርግለት፤ በዚህና በዚያ በሁለቱ ጎን ታደርጋቸዋለህ፤ በእነርሱ እንዲሸከሙም የመሎጊያዎቹ ማስገቢያ ይሁኑ።
የነዌም ልጅ ኢያሱ ካህናቱን ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “የቃል ኪዳኑን ታቦት አንሱ፥ ሰባትም ካህናት ሰባት ቀንደ መለከት በጌታ ታቦት ፊት ይሸከሙ።”