ሐዋርያት ሥራ 20:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፤ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም በመርከብ ተጕዘን ከኪዩ ደሴት ትይዩ ደረስን። በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞን ተሻገርን፤ በማግስቱም ሚሊጢን ደረስን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ከዚያ ተነሥተን በኪዮስ ፊት ለፊት ወዳለው ስፍራ በመርከብ ደረስን፤ በሚቀጥለውም ቀን ወደ ሳሞስ ተሻገርንና በማግስቱ ወደ ሚሊጢ ደረስን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በማግሥቱም ከዚያ ወጥተን በኪዮስ ፊት ለፊት ደረስን፤ በማግሥቱም ወደ ሳሞስ አለፍን፤ በትሮጊሊዮም ተቀመጥን፤ ከዚህ ቀን በኋላም ወደ መሊጡ ደረስን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በማግሥቱም ከዚያ በባሕር ተነሥተን በኪዩ ፊት ለፊት ደረስን፥ በነገውም ወደ ሳሞን ተሻገርን በትሮጊሊዮም አድረን በማግሥቱ ወደ ሚሊጢን መጣን። |