2 ሳሙኤል 20:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አማሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ሰይፍ መኖሩን ልብ ስላላለ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ስለዚህ ኢዮአብ ሰይፉን ሆዱ ላይ ሻጠበት፤ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ መድገምም አላስፈለገውም፥ አማሳይ በዚያው ሞተ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ፥ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደድ ጀመሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ሰይፍ መኖሩን ልብ ስላላለ ጥንቃቄ አላደረገም፤ ስለዚህ ኢዮአብ ሰይፉን ሆዱ ላይ ሻጠበት፤ አንጀቱም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ከዚያም ኢዮአብ መድገም ሳያስፈልገው፣ አሜሳይ በዚያው ሞተ። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ፣ የቢክሪን ልጅ ሳቤዔን ማሳደድ ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአብ በሌላው እጁ የያዘውን ሰይፍ ስላላየ ዐማሣ አልተጠነቀቀም ነበርና ኢዮአብ በሆዱ ሻጠበት፤ የሆድ ዕቃውም መሬት ላይ ተዘረገፈ፤ ወዲያውኑ ስለ ሞተም ኢዮአብ በድጋሚ አልወጋውም። ከዚህ በኋላ ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳ የቢክሪን ልጅ ሼባዕን ማሳደዳቸውን ቀጠሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፤ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፤ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፤ ሁለተኛም አልወጋውም፤ ሞተም። ኢዮአብና ወንድሙ አቢሳም የቢኮሪን ልጅ ሳቡሄን አሳደዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሜሳይ ግን በኢዮአብ እጅ ከነበረው ሰይፍ አልተጠነቀቀም ነበር፥ ኢዮአብም ሆዱን ወጋው፥ አንጀቱንም በምድር ላይ ዘረገፈው፥ ሁለተኛም አልወጋውም፥ ሞተም። |
አሣሄል ግን ማሳደዱን አልተወም፤ ስለዚህ አበኔር በጦሩ ጫፍ ሆዱን ወጋው፥ ጦሩም በጀርባው በኩል ወጣ፤ አሣሄልም እዚያው ወደቀ፤ ወድቆም በነበረበት ስፍራ ሞተ። እያንዳንዱም ሰው አሣሄል ወድቆ ወደ ሞተበት ስፍራ ሲደርስ ይቆም ነበር።
አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።
የናታንያም ልጅ እስማኤል ከእርሱም ጋር የነበሩት አሥሩ ሰዎች ተነሥተው የሳፋንን ልጅ የአኪቃምን ልጅ ጎዶልያስን በሰይፍ መቱ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በአገሩ ላይ የሾመውን ገደሉ።
እስራኤላውያን እንደገና ወደ ጌታ ጮኹ፤ ጌታም ብንያማዊውን የጌራን ልጅ፥ ግራኙን፥ ኤሁድን ነጻ እንዲያወጣቸው አስነሣው። እስራኤላውያን ኤሁድን ግብር አስይዘው ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ ዔግሎን ላኩት።
አቢሳም ዳዊትን፥ “ዛሬ እግዚአብሔር ጠላትህን በእጅህ ላይ ጥሎታል፤ አሁንም እኔ አንድ ጊዜ በጦር ወግቼ ከመሬት ጋር ላጣብቀው፤ መድገምም አያስፈልገኝም” አለው።