2 ዜና መዋዕል 6:39 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በማደሪያህ በሰማይ ሆነህ ስማ፥ ፍርድንም አድርግላቸው፤ በአንተም ላይ ኃጢአት የሠሩብህን ሕዝብህን ይቅር በል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከማደሪያህ ከሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውንና ልመናቸውን ስማ፤ ፍረድላቸውም። የበደሉህንም የሕዝብህን ኀጢአት ይቅር በል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጸሎታቸውን ስማ፤ በመኖሪያህ በሰማይ ሆነህ ጸሎታቸውን በመስማትም ምሕረት አድርግላቸው፤ የሕዝብህን ኃጢአት ሁሉ ይቅር በል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በተዘጋጀ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ፍርድንም አድርግላቸው፤ አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን ይቅር በል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸሎታቸውንና ልመናቸውን በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ ፍርድንም አድርግላቸው፤ አንተንም የበደሉህን ሕዝብህን ይቅር በል። |
በተማረኩበትም በምርኮአቸው አገር ሳሉ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው ወደ አንተ ቢመለሱ፥ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠሃት ወደ ምድራቸው ወደ መረጥሃትም ከተማ ለስምህም ወደ ሠራሁት ቤት ቢጸልዩ፥