1 ጢሞቴዎስ 3:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈጥኜ ወደ አንተ ለመምጣት ተስፋ በማድረግ ይህን ጽፌልሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ አንተ ቶሎ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም ይህን ትእዛዝ እጽፍልሃለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቅርብ ጊዜ ለመምጣት ተስፋ ባደርግም እንኳ ምናልባት ከመምጣት የዘገየሁ እንደ ሆነ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያንና የእውነት ዐምድ መሠረት በሆነው በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ሰዎች ምን ማድረግ እንደሚገባቸው ታውቅ ዘንድ ይህን መመሪያ እጽፍልሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈጥኜ ወደ አንተ እንድመጣ ተስፋ አድርጌ ይህን እጽፍልሃለሁ። |
ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።
ብዙ የምጽፍላችሁ ነገር ነበረኝ፤ ነገር ግን በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልፈለግሁም፤ ዳሩ ግን ደስታችን ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ መጥቼ ፊት ለፊት ላናግራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።