አሣሄልንም ከወደቀበት አንሥተው በቤተልሔም በሚገኘው በአባቱ መቃብር ቀበሩት። ከዚያም ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሡ አድረው፥ ኬብሮን ንጋት ሆነ።
1 ሳሙኤል 17:58 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም፣ “አንተ ወጣት፣ የማን ልጅ ነህ?” ሲል ጠየቀው። ዳዊትም፣ “እኔ የአገልጋይህ የቤተ ልሔሙ ሰው የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “አንተ ወጣት የማን ልጅ ነህ?” ብሎ ጠየቀው። ዳዊትም “የቤተልሔም ነዋሪ የሆነው የአገልጋይህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ሲል መለሰለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም፥ “አንተ ብላቴና የማን ልጅ ነህ?” አለው ዳዊትም፥ “እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ” ብሎ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም፦ አንተ ብላቴና፥ የማን ልጅ ነህ? አለው። ዳዊትም፦ እኔ የቤተ ልሔሙ የባሪያህ የእሴይ ልጅ ነኝ ብሎ መለሰ። |
አሣሄልንም ከወደቀበት አንሥተው በቤተልሔም በሚገኘው በአባቱ መቃብር ቀበሩት። ከዚያም ኢዮአብና ሰዎቹ ሌሊቱን ሁሉ ሲገሠግሡ አድረው፥ ኬብሮን ንጋት ሆነ።
ጌታ ሳሙኤልን፥ “በእስራኤል ላይ እንዳይነግሥ ለናቅሁት ለሳኦል የምታለቅስለት እስከ መቼ ነው? ወደ ቤተልሔሙ ሰው ወደ እሴይ ስለምልክህ፥ ዘይት በቀንድ ሞልተህ ሂድ፤ ከልጆቹ አንዱ ንጉሥ ይሆን ዘንድ መርጬዋለሁ” አለው።
ዳዊት፥ በይሁዳ ስምንት ወንዶች ልጆች የነበሩት፥ የቤተልሔሙ ሰው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይም በሳኦል ዘመን ያረጀና ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር።
አባትህ ከፈለገኝ፥ ‘ለቤተ ዘመዶቹ ሁሉ ዓመታዊ መሥዋዕት የሚቀርብ ስለሆነ፥ ዳዊት ወደ መኖሪያ ከተማው ወደ ቤተልሔም ቶሎ ለመሄድ አጥብቆ ፈቃድ ጠየቀኝ’ ብለህ ንገረው።