ይህ ነገር ከተደረገ በኋላ የአምራይ ልጆች ትልቅ የጋብቻ በዓል የሚያደርጉ መሆናቸውን ለዮናታንና ለወንድሙ ለስምዖን ተነገራቸው፤ ሙሽራይቱን ከናዳባት (ከናባታ) በታላቅ ክብር ያመጡ ነበር። እርሷ የአንድ በከነዓን አገር የተከበረ ሰው ልጅ ነበረች።