በእያንዳንዱ ዝሆን ላይ በጠፍር ጥብቅ ተደርጐ የታሰረ ጠንካራ የእንጨት ቤት እንደ መከላከያ ምሽግ ሆኖ ተሠርቶለት ነበር። በውስጡም ተመድበው የሚያገለግሉ ሶስት ተዋጊ ወታደሮችና አንድ የዝሆን ጠባቂ ይገኛሉ።