ስምዖን የይሁዳን አገር ምሽጐች እንደገና ሠራቸው፤ በዙሪያቸው ረዣዥም የግንብ ምሽጐችን ሠራ፤ መዝጊያዎችና መቆለፊያዎች ያሏቸው ታላላቅ መካባቢያዎችንም ሠራ፤ በምሽጐቹ ውስጥ ስንቅ አስገብቶ አስቀመጠ።