ንጉሥ ዲሜጥሮስ በሥሩ ያለው አገር በሰላም የሚገኝ መሆኑንና ሥልጣኑን የሚቃወም ምንም አለመኖሩን በማየት ሠራዊቱን ሁሉ አሰናብቶ እያንዳንዳቸው ወደመጡበት እንዲሄዱ አደረገ፤ ከእርሱ ጋር የቀሩት ከአሕዛብ ደሴት የቀጠራቸው የውጭ አገር ወታደሮች ብቻ ነበሩ።