በሌላ በኩል ከዛሬ ጀምሮ ከመሬት ፍሬ የሚሰጠውን ሲሶ ለሁልጊዜ ትቻለሁ፤ ከዛፎች ፍሬ የሚደርሰኝንም እኩሌታ ትቻለሁ፤ ይህን ያደረግሁት ለይሁዳ አገርና ከሰማርያና ከገሊላ ለተጨመሩለት ለሦስቱም አገሮች ነው።